Friday, February 23, 2018

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምዕራባዊያን ትክክል፤ ለድሀ አገራት ስህተት ሊሆን አይችልም

(Feb 23, (ኢትዮጵያ ))--የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀውስ ማብረጃ፣ የአገርንና ዜጎችን ደህንነት ማስጠበቂያ ህገመንግስታዊ አሰራር ነው። በበለጸጉት አገራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲተገበር የመብት ተከራካሪ ነን የሚሉ ድርጅቶች ሲከሷቸው ወይም ሲወነጅሏቸው ተመልክተን አናውቅም። (Feb 23, (ሁሌም የሚወነጅሉት ታዳጊ አገራት በተለይ ከምዕራባዊያን የተለየ አይዲዮሎጂ (ርዕዮተዓለም) የሚያራምዱ አገራትን ነው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የዴሞክራሲ ተምሳሌት ተደርገው በሚወሰዱ አገራት ሳየቀር በተለያዩ ጊዜያት ታውጆ አይተናል። አሜሪካ መስከረም 11ቀን 2000 የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አውጃለች። የሚገርመው አሁንም ድረስ በዚሁ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ መሆኗ ነው።

ፈረንሳይ በአስር ዓመታት ውስጥ አይታ በማታውቀው ደረጃ በጣም አሰቃቂው የሽብር ጥቃት በደረሰባት ወቅት በአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፍራንሴስ ሆላንዴ አማካይነት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሳቢያም በፈረንሳይ ከተሞችና አለም ዓቀፍ ኤርፖርቶች እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ሰራዊቶችን ማየት በጣም የተለመደ ተግባር ነው። አገሪቱ አሁንም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች፡፡ ቱርክ በፕሬዚዳንት ታይብ ኤርዶጋን ላይ በተቃጣው የመንግስት ግልበጣ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። አሁንድረስ ቱርክ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ናት፡፡

ቱንዚያ፣ ማሊ፣ ቬንዙዌላ፣ ዩክሬን፣ ሩሲያ፣ ግብጽ፣ ሶሪያና አልጀሪያም ሌሎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ የሚገኙ አገራት ናቸው።  አገራት በአንድም በሌላ የቀደመው ሰላማቸው ሲናጋና በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርዓት ያንን መፍታት ሳይችሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን መፍትሄ አድረገው ያቀርባሉ። ከላይ የተመለከትናቸው አገራት ተሞክሮም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው።  እወነታው ይሄ ቢሆንምና ምዕራባዊያንም በዚህ አዋጅ እየተተገለገሉ ሳለ፤ በአፍሪካ (ታዳጊ አገራት) አዋጁ ተግባራዊ ሲሆን ከተለያዩ ጉዳዮች ጋር የሚያያዝበት ምክንያት ግልጽአይደለም።

ወደ አገራችን ስንመጣም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅ የሚችልበት አጋጣሚ እንደሚኖር በኢፌዲሪ ህገመንግስት በግልጽ ተደንግጓል። አሁን በይፋ የታወጀው አዋጅ ምንነቱ፣ አስፈላጊነቱ፣ ህገመንግስታዊና አለም አቀፋዊ መርሆዎችን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ግን እንደ አሜሪካ ላሉ አገራትና የአውሮፓ ህብረት የሚዋጥ አይደለም። ስለሆነም አይናቸውን በጨው አጥበው ለምን ታወጀ ሲሉ ይሞግታሉ። ይሄ ባለሁለት ፈርጅ አካሄድ እንደሆነ እነሱም ያውቃሉ እኛም አላጣነውም።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሃብታም አገራት ሲሆን ቀውስ ማስወገጃ፤ ዜጎቻቸውን ከከፋ ጉዳት መታደጊያ ተደርጎ ይወሰዳል። ለደሃ አገር ሲሆን ደግሞ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ተደርጎ መወሰዱ አግባብነት የጎደለውና የተዛነፈ አስተሳሰብ መሆኑን መረዳት የሚከብድ አይደለም።

የዚህች አገር መፍትሄው ያለው አዚሁ አገር ቤት ውስጥ ባሉት ዘጎቿ እንጂ አገርን በተለያየ መንገድ ጥለው በኮበለሉ እና በድሃዋ ልጅ ህይወት በሚቆምሩ ተስፈኛ ተሸናፊ ፖለቲከኞች፤ ብሎም የዚህችን አገር ከፍታ በማይፈልጉ አካላት ሊሆን አይገባም።
(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
 

No comments:

Post a Comment