Thursday, November 09, 2017

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሃገሪቱ ልማት ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እያደገ መጥቷል- ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

(ጥቅምት 30, (ኢብኮ))-- በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታና በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚያደርጉት ተሳትፎ እያደገ መጥቷል፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የየክልሎችን የዲያስፖራ ጽ/ቤት ሀላፊዎችና የፌዴራል የዲያስፖራ አደረጃጀቶችን የሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ተገምግሟል፡፡



በግምገማው ወቅት እንደተገለጸው ባለፉት 3 ወራት በሀገሪቱ 171 የዲያስፖራ አባላት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ፈቃድ የወሰዱ ሲሆን 45ቱ ወደስራ ገብተዋል፡፡ የዲያስፖራ አባላቱ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ660 ሺ ዶላር በላይ ቦንድ ግዢ መፈጸማቸውንም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደመቀ አጥናፉ ተናግረዋል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው አያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ እያደገ መምጣቱን የተናገሩት ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር አክሊሉ ሀ/ሚካኤል ናቸው፡፡

ዲያስፖራው ለኢኮኖሚው ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል፡፡ በውጭ ከሚኖሩ የዲያስፖራ አባላት ባለፈው አመት ከ4 ነጥብ 6 ቢልዮን ዶላር በላይ ወደሀገር ቤት ተልኳል፡፡

የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅሞች በሚያስከብሩ ጉዳዮች ላይ አባላቱ የሚያደርጉት ተሳትፎ አያደገ መምጣቱም በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

No comments:

Post a Comment