Monday, September 25, 2017

በአፍሪካ በትልቅነቱ ቀዳሚ የሆነው መስቀል በመቀሌ አካባቢ ተተከለ፡፡

(መስከረም 14፣2010, (መቐለ))--መስቀሉ የመቐለ ሕዝበ ክርስቲያን የመስቀል በዓል በሚያከብሩበት በጮምአ ተራራ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ ተመርቋል፡፡ ፓትርያርኩ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት መስቀል የሰላም ምልክት በመሆኑ ሁሉም ትኩረት እንዲሰጥ ለምዕመኑ አሳስበዋል፡፡


በዊነር ኢንደስትሪያል ኢንጅነሪንግ የተሰራው ይህ መስቀል 52 ሜትር ቁመት ሲኖረው ክብደቱ 53 ሺህ ኪሎ ግራም እንደሚመዝን ተገልጿል፡፡ የመስቀሉ መሠራት ከመንፈስዊ ይዘቱ ባሻገር ለኢኮ ቱሪዝም እንቅስቃሴው ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም የመቐለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
 
የከተማዋ ነዋሪዎች በመስቀሉ መተከል ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ አካባቢውን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ መግለፃቸውንም ሪፖርተራችን ብሩክ ተስፋዬ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

2 comments:

Unknown said...

HA,Ha Ha,HA since when the devil build cross

Unknown said...

Yetegre pop is the devil son himself

Post a Comment