Tuesday, November 01, 2016

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲስ የካቢኔ አባላትን ሹመት አጸደቀ

(ጥቅምት 22፣2009, (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ))--የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበውን  አዲስ የካቢኔ አባላትን ሹመት አጸደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ባካሄደው 5ተኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ተኛ መደበኛ ሥብሰባውን ኢህአዴግ የመንግስትን ስልጣን በተገቢው ደረጃ ለህዝብ አገልግሎት ለማዋልና የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ በጥልቀት ለመታደስ የጀመረውን ሂደት መሠረት በማድረግ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ያቀረቡት የአስፈፃሚ አካላትን ሹመት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የካቢኔ ሚንስትሮች ሹመት መሰረት ያደረገው ውጤታማነትን፣ ለህዝብ ወገንተኝነትና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ቀደም ሲል የነበረው በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማእረግ በክላስተር የማስፈፀም እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሚሉ ቦታዎች ሙሉ በሙሉ መቅረታቸውን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሉበት ይቀጥላሉ ያሏቸው የካቢኒ አባላት፦
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው፣ የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ይናገር ደሴ እና የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ናቸው።
አዲስ እየቀረቡ ካሉት እጩ የካቢኒ አባላት መካከል፦

1. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፦ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር

2. አቶ ታገሰ ጫፎ፦ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ሚንስትር

3. ዶክተር አብረሃም ተከስተ፦ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስትር

4. ዶክተር በቀለ ጉላዶ፦ የንግድ ሚንስትር

5. ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፦ የእንስሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚንስትር

6. ዶክተር ኢያሱ አብረሃ፦ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስትር

7. ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስትር

8. አቶ አህመድ ሺዴ፦ የትራንስፖርት ሚንስትር

9. ዶክተር አምባቸው መኮንን፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስትር

 10. ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፦ የኮንስትራክሽን ሚንስትር

11. ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፦ የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚንስትር

12. አቶ ሞቱማ መቃሳ፦ የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር

13. ዶክተር ገመዶ ዳሌ :-የአከባቢ ደንና አየረ ለውጥ ሚንስትር

14. ዶከተር ሽፈራው ተክለማርያም :-የትምህርት ሚንስትር

15. ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ:- የጤና ጥበቃ ሚንስትር

16 . ዶክተር ግርማ አመንቴ :- የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚንስትር

17 .ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም:- የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር

18 . ወይዛሮ ደሚቱ ሀምቢሳ:- የሴቶችና ህጻናት ሚንስትር

19. አቶ ርስቱ ይርዳው :-የወጣቶችና ስፖርት ሚንስትር

20 .አቶ ከበደ ጫኔ:- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ ሚንስትር

21 , ዶክተር ነገሪ ሌንጮ :- የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሀላፊ ሚንስትር አድርገው አቅርበዋል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረቡት የካቢኔ አባላት ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽደቋል፡፡

በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቃለ-መሃላ ከፈፀሙት 21 የካቢኔ አባላት መካከል ሶስቱ ሴቶች ናቸው።
ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

No comments:

Post a Comment