Sunday, February 01, 2015

«ዳያስፖራው ለአሉቧልታዎች ቦታ የለውም» -ሼክ ሳልሃዲን ወዚር

(ጥር 24/2007, (አዲስ አበባ))-- በመላው ዓለም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልኡካን ቡድን በቅርቡ በሀገሪቱ ባካሄዱት ጉብኝት «ሃይማኖቶች ላይ ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር ባህላችንን አሁንም ማስጠበቅ ይኖርብናል» በማለት ገልፀዋል።

የልኡካን ቡድኑ አባላት ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ከዶክተር አህመድ አብዱራህማን ጋር በኡማ ሆቴል በሃይማኖት መቻቻል እና በእስልምና ሃይማኖት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። በሁሉም ሃይማኖቶች ዘንድ ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር ባህልን አሁንም ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግም በውይይቱ ወቅት ተገልጿል ።

የልኡካን ቡድኑ አባል ከሆኑት መካከል ሼክ ሳልሃዲን ወዚር ከአዲስ አበባ እስልምና ምክር ቤት ጉዳዮች ፕሬዚዳንት ጋር በእስልምና ሃይማኖት ዙሪያ ያደረጉት ውይይት በጣም እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል። አንዳንድ ፀረ ሰላም ሃይሎች ሀገሪቷ የምትታወቅበትን የሃይማኖት መቻቻል ለማደፍረስ እንዲሁም የተጀ መሩትን ልማቶች ለማደናቀፍ የሚያ ደርጉትን ጥረት እንደሚነቅፉና እንደ ሚታገሉ ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት አስተያየት አስታው ቀዋል። ሙሉ አስተያየታቸውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

እዚህ የመጣነው የልኡካን ቡድን ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ሀገሮች የምንኖር በሀገራችን ኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግና መዋዕለ ንዋያችንን ለማፍሰስ ተወካዮቹን ወደዚህ የላከ የልኡካን ቡድን ነው።

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከክቡር ፕሬዚዳንቱን ጀምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎችም ከፍተኛ ባለስልጣኖች አቀባበል አድርገውልናል። በኢንቨስትመንት ዙሪያም ተወያይተናል። በዚህ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለፃ ተሰጥቶናል።

ከዚህም ሌላ ሙሉው የልኡካን ቡድኑ ወደ ህዳሴ ግድብ ሄደን ታሪካዊና ሀገራችንን ከዳር እስከዳር ያነቃነቀ የህዳሴ ግድብ በቦታው ተገኝተን አይተናል። በቴሌቪዥን ማየትና በአካል መመልከት በጣም ልዩነት አለው። በቦታው ተገኝተን ያየነው በእውነቱ ወገኖቻችን ቦታው ላይ ሆነው ሲሰሩ አይተናል። ከኢንጂነር ስመኘው በቀለ በጣም ጥልቀት የተሞላበት ትንታኔ ተሰጥቶናል ከልባችንም ማርኮናል፤ በጣምም አስደስቶናል። ይህ ፕሮጀክት በማንኛውም በአላት ስራው የማይቆም ነው። ከምሽቱ አምስት ሰአት ደርሰን በተመለከትንበትም ወቅት ማሽኖቹና ሰራተኞቹ 24 ሰአት እየሰሩ ያሉትን እንቅስቃሴ በአይናችን አይተን በምስልም ቀርፀን ይዘናል። በቂ ማብራሪያዎችም ሰጥተውናል።

ይህ የልኡካን ቡድን በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ አማራጮችን ሁሉ አይተን ሶስት ዋና ዋና ዘርፎችን መርጠን በነሱ ላይ ለመስራት ወስነናል። አንደኛው በኢንዱስትሪው ዘርፍ ስራ አጡ ሰርቶ እንጀራ ያገኝ ዘንድ ቲማቲም ፋብሪካ ለመገንባት ለይተናል። ቦታውንም ለማደስና ስራውን ለመጀመር ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ሌላው ደግሞ የሚስማርና የቀለም ፋብሪካ ለመገንባትና ወደስራ ለመግባት ፍላጎት አለን። ሶስተኛው ደግሞ በግብርና ዙሪያ እንዲሁም በመኖሪያ ቤት ግንባታ ዙሪያ ለመሰማራት አቅደናል። በዚህ ዙሪያ የከተማ ልማት ሚኒስትሩንም እንዲሁም የከተማውን ከንቲባ ለማግኘትና በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ዝግጀት ላይ እንገኛለን። በግብርናው ዘርፍ ላይም እስከ ደብረብርሃን ድረስ በመሄድ እንዲሁም የግብርና ሚኒስትሩን በማነጋገር ሰፊ ስራዎች እየሰራን እንገኛለን።

በእውነቱ ኢትዮጵያ የእድገት ማእበል ላይ እንዳለችና በከፍተኛ ደረጃ ለውጥ እያመጣች ያለች ሀገር መሆኗን በአካል ተገኝተን መስክረናል። የባቡር ሃዲድ ዝርጋታው የቀላል ባቡር በአካል በመሄድ ጉብኝት አድርገናል። እንዲሁም የአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ ጎብኝተን የተሰራበትን ሁኔታ የገንዘቡን ምንጭ አይተን ተረድተናል።

የ2007 ምርጫ መጀመርን ተከትሎ አስር ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 20 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎቻችን ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ተመዝግበው እንደሚገኙ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ሂልተን ተገኝተን ማብራሪያ ሰጥተውናል። ሀገራችን የሰላም እሴት የመረጋጋት እሴት መሆኗን በተግባር አይተን መስክረናል።

ከአዲስ አበባ ከፍተኛ ምክር ቤት ከየክፍለ ከተማው ያሉ የሙስሊም የሃይማኖት አባቶች እኛ በዳያስፖራ የምንገኝ በሀገር መረጋጋትና በፀረ ሽብርተኝነት ትግል ዙሪያ የሚነዙትን አሉባልታዎች በፍፁም እንደማያስተናግዱና አክራሪዎችን እንደሚዋጉና ከዚህ በፊትም መክተው ሽብርተኝነትን እንደተቆጣጠሩ፤ ወደፊትም ለመመከት በውይ ይታችን ላይ ቃል ገብተውልናል።

ሀገራችን እንደሶሪያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ የእልቂት መድረክ በሃይማኖት ዙሪያ ያመጡትን መዘዞች እንደ ቦኮሃራም እና አይ ኤስ አይ ኤስ ይህንን የሰጣናዊ አስተምሮት፤ የውሃቢዝም የምንላቸው የሳውዲዓረቢያ የነዳጅ ገንዘብ ያሰከራቸው ሃይሎች ሀገራችን መጫወቻ እንደማትሆን እኚህ የሃይማኖት አባቶች ፀንተው እንደሚታገሉ በማየት እኛም ይህንን ደግፈናል።

በምርጫ ያላገኙትን በአምባገነንነት የኢትዮጵያ ፌዴራል መጅሊስ ጥቂት ግለሰቦች አፍነውት ህዝብ የመረጠውን ያለምንን የህግ ሥርዓት ለማፍረስ ጥረት የሚያደርጉትን መንግስት ሥርዓት እንዲያሲይዛቸው እኛና የልኡካን ቡድኑ ጠይቀናል። በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ፌዴራል መጅሊስን የሚያተራምሱ፣ የአክራሪዎችን መንደርደሪያና የአይ ኤስ አይ ኤስ አስተሳሰብ ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባትና ለማተራመስ ጥረት የሚያደርጉት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እየጠየቅን እንገኛለን። ይህ ሀገራችንን ወደ እልቂት እንዳያመጣ አደጋውም የከፋ መሆኑን ተገንዝበን የምንደራደርበት ጉዳይ እንዳልሆነ በግልፅ ሊታወቅ ይገባል። በህዝብ መሃል እንዴት ሰርገው እንደገቡ፤ማን ወደዚህ እንዳ መጣቸውም ይሄ ወደፊት መጠየቅ ያለበት ጉዳይ ነው ብለን ማሳሰብ እንወዳለን። ሀገራችን የማንም መጫወቻ እንዳትሆን ሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን። ሰላም ሲባል ደግሞ ቀጣይነት ያለው ሰላም የማየት ፍላጎታችንም ትግላችንም ጥያቄያችንም ነው።

ሰላም ከሌለ ምንም የለም። ሰላም ከሌለ ትምህርት ቤት መሄድ የለም። ሰላም ከሌለ ምናልባት መስገድም ላይመች ይችላል። ሰላም ከሌለ ቤተክርስቲያን መሄድ ላይኖር ይችላል። በአጠቃላይ ሰላም ከሌለ ምንም የለም። እነዚህ የሰላም ነቀርሳ የሆኑት እንደ ቦኮሃራም ዓይነቶቹ የጥፋት ሃይሎች ሁለት መቶ የሚሆኑ ሴት ህፃናት ጠልፈው «ሚስቶቼ ናቸው፣ ባሮቼ ናቸው» ብሎ አፀያፊ ነገር የሚያደርገው ወደኛ ሊመጣ ቀርቶ በዓለም ላይ ሊጠፋ የሚገባ ነው። የእስልምና ሃይማኖትን የማይወክል በመሆኑም በህዝበ ሙስሊሙ ስም እናወግዛለን። ኢትዮጵያ የማንም መጫወቻ አትሆንም።

እኚህ በሶፊያ ሞደሬት ዘላቂ ሰላም ያሰፈነ ሊደገፍ ይገባል። የሚያሳዝነው እነዚህ በአክራሪ ዙሪያ ውሃቢስቶቹ ካላቸው የአፍሪካ ቲቪ ፕሮፓጋንዳ ባሻገር አንዳንድ ጊዜ የመንግስትን ሚዲያ በተለያዩ ምክንያቶች ለማፈን የሚያደደርጉት ጥረት ሊቆም ይገባል እንላለን። ሚዲያ ያለውን መረጃ ሳይታፈን ለህዝቡ መድረስ አለበት። ስጋችንን ከዚህ ብንለይም ከናንተው ከወገኖቻችን ጋር እንዳለን ሁልጊዜ እንድታውቁልን እንፈልጋለን። ኢትዮጵ ያችን፣ አለማችን ሰላም ይሁን ሙስሊም ክርስቲያኑ ተቻችሎ ተከባብሮ አብሮ ለመኖርና ለሌሎቹ ምሳሌ እንሁን እላለሁ አመሰግናለሁ።
ምንጭ: ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ 

No comments:

Post a Comment