Saturday, September 01, 2012

በመለስ ሽኝት ዋዜማ

(Sept 01, 2012, Reporter)--የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብሔራዊ ሥርዓተ ቀብር በመጪው እሑድ ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም. በታላቅ ሥነ ሥርዓት በመንበረ ፀባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 

ሐሙስና ዓርብ ከምሽቱ 11 ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ድረስ በመስቀል አደባባይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሻማ እያበሩ አበባ በማስቀመጥ ሐዘናቸውን የሚገልጹበት ሥነ ሥርዓት ለማከናወን ፕሮግራም ሲያዝ፣ ቅዳሜ ዕለት ደግሞ በእምነት ተቋማት አማካይነት ሙሉ የሐዘን ቀን እንደሚሆን ታውቋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎችና ክልሎች የተለያዩ ፕሮግራሞች ይካሄዳሉ፡፡

እስካለፈው ማክሰኞ ድረስ የ20 አገሮች መሪዎች በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎችም ይገኛሉ ተብሏል፡፡ ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓቱን የሚመራው ኮሚቴ የተለያዩ መርሐ ግብሮችን በተከታታይ እንደሚገልጽ አስታውቋል፡፡
Source: Reporter
 Home

No comments:

Post a Comment